1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የትንሳኤ በዓል ዋዜማ በመቀሌ ደምቋል

ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 26 2016

ለሁለት ወራት በዓብይ ፆም ላይ የቆየው ህዝበ ክርስቲያን በነገው ዕለት የትንሳኤ በዓል ለማክበር በዋዜማው ላይ ይገኛል። ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ መቐለ፥ በዓል ዋዜማ ግብይት እና የተለያዩ ስነስርዓት ደምቃለች።

https://p.dw.com/p/4fVTh
Äthiopien Mekele 2024 | Viehmarkt zum äthiopischen Osterfest während der Unruhen in Amhara
ምስል Million Hailesilasie/DW

በትግራይ የበዓል ዋዜማው ደማቅ ቢሆንም የዋጋ ንረቱ አያስቀምስም

መቐለ በበዓል ዋዜማው ደምቃለች። የበዓል ግብይቱ ደርቷል፣ ከተማው ሞቅ ደመቅ ብሏል። የገበያ ንረቱ ግን በርካቶች አሳስቧል።

ለሁለት ወራት በዓብይ ፆም ላይ የቆየው ህዝበ ክርስቲያን በነገው ዕለት የትንሳኤ በዓል ለማክበር በዋዜማው ላይ ይገኛል። ዛሬ ከጠዋት ጀምሮ መቐለ፥ በዓል ዋዜማ ግብይት እና የተለያዩ ስነስርዓት ደምቃለች። ተዘዋውረን በተመለከትናቸው የመቐለ የገበያ ስፍራዎች ለእርድ የሚሆኑ በጎችና ፍየሎች፣ ደሮ እና የተለያየ አስቤዛ፣ የስጦታ እቃዎች፣ የህፃናት እና አዋቂዎች ልብስ ግብይት በስፋት ይታያል።

መቀሌ ውስጥ የትንሳኤ በዓል የዶሮ ገበያ
ለሁለት ወራት በዓብይ ፆም ላይ የቆየው ህዝበ ክርስቲያን በነገው ዕለት የትንሳኤ በዓል ለማክበር በዋዜማው ላይ ይገኛልምስል Million Hailesilasie/DW

በዓለ ስቅለትና የትንሳኤ ገበያ

በአንፃራዊ ሰላም ላይ ሆነው በዓሉ የሚያከብሩ ያነጋገርናቸው የመቐለ ነዋሪዎች፥ የኑሮ ውድነቱ የገበያ ንረቱ ግን አማሯቸዋል። የበዓል ዋዜማው ከግብይት እና የተለያዩ የመዝናኛ ፕሮግራሞች ውጭ በከተማይቱ የተለያዩ እምነት ተከታይ አብያተክርስቲያናትም እንዲሁ መንፈሳዊ ስነ ስርዓቶች እየተከወኑ ነው።

ሚሊዮን ኃይለስላሴ

ታምራት ዲንሳ